
ባሕር ዳር: መጋቢት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ከነገ ጀምሮ የሚያደርገውን የአጀንዳ ማሠባሠብ ሥራ አስመልክቶ መግለጫ እየሰጠ ነው።
መግለጫውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ.ር) እና ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም እየሰጡ ነው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ከነገ መጋቢት 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ አጀንዳ ያሠባሥባል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ለጋራ ሀገር በጋራ መሥራት አለብን ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል የተለያዩ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱንም ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታ ማጠናቀቁን ተከትሎ ከነገ ጀምሮ የአጀንዳ ማሠባሠብ ሥራውን ይቀጥላል ነው ያሉት።
ወኪሎች በተገኙበት የአጀንዳ ማሠባሠብ ሥራው ነገ ጀምሮ ለቀናት ይቆያል ነው ያሉት። ተሳታፊዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
