
አዲስ አበባ: መጋቢት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “የወጣቶችን አቅም ለበለጸገች አፍሪካ” በሚል መሪ መልዕክት የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
በጉባኤው ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አፍሪካውያን ወጣቶች እና መሪዎች ከመሠብሠብ ባለፈ ለተግባራዊ ለውጥ እንዲተጉ አሳስበዋል።
በኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን ምሳሌ የሚኾኑ የአረንጓዴ አሻራ፣ የሌማት ትሩፋት እና ሌሎች የልማት ሥራዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።
ወቅቱ የለውጥ ወቅት እንደኾነም ተናግረዋል። አፍሪካውያን መሪዎች እና ወጣቶች ለለውጥ አንድ ኾነው እንዲሠሩም አሳስበዋል።
በጉባኤው የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ስታርታፖች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶቻቸውን በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ላይ አስተዋውቀዋል።
በአውደ ርዕዩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በተጨማሪ የፌዴራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የፓን አፍሪካ ወጣት መሪዎች እና ሌሎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ አበበ ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
