ወጣት አፍሪካውያንን ለአሕጉሪቱ ልማት የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ዓላማው ያደረገ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

30

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ‎አፍሪካዊ ወጣቶችን ለልማት መጠቀም ላይ መሰረት ያደረገ የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባዔ ነው ዛሬ በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ የሚገኘው።

“የወጣቶችን አቅም ለበለፀገች አፍሪካ” በሚል መሪ መልዕክት ነው በኢትዮጵያ ለመጀመሪ ጊዜ ጉባኤው የሚካሄደው፡፡

በጉባኤው ከአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት መሪዎች እና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ወጣት ምሁራን፣ ወጣት የማኅበረሰብ አንቂዎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እየተሳተፉ ነው፡፡

የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚካሄድ ነው።

ዘጋቢ፦ አበበ ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በብሔራዊ የምግብ ሥርዓት ስትራቴጂዎች ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው።
Next articleበጎንደር ከተማ የከተማ አውቶብሶች ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ መኾናቸው ተገለጸ።