
ባሕር ዳር: መጋቢት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የግብርና ልማቱን ያፋጥናሉ በተባሉ:-
👉በብሔራዊ የምግብ ደኅንነት እና ጥራት ስትራቴጂ ለተቀዳሚ ለተቀዳሚ የግብርና ምርቶች፣
👉 ብሔራዊ የድኅረ ምርቶች አያያዝ ስትራቴጂ እና
👉 በብሔራዊ የምግብ ሥርዓት ስትራቴጂዎች እንዲሁም ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ ላይ የማስተዋወቂያ መድረክ አዘጋጅቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው።
በመድረኩ በፌዴራል ግብርና ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀሚድ ጀማል (ዶ.ር) እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አጀበ ስንሻውን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል የግብርና እና የባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
