
ባሕር ዳር: መጋቢት 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለጣና ፎረም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ውይይት ባሕር ዳር የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዴዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) እና አምባሳደሮች የባሕር ዳር ከተማ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ላይ ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) እና ሌሎችም የክልሉ መሪዎች ተገኝተዋል።
መሪዎቹ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በጣና ሐይቅ ዙሪያ የሚሠሩ የጎብኝዎች መዳረሻ ቦታዎችን ተመልክተዋል። የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕንጻ የእድሳት ሥራዎችንም ጎብኝተዋል።
ባሕር ዳር ሰላሟን አስጠብቃ በልማት ላይ የምትገኝ ውብ ከተማ መኾኗንም መሪዎቹ ገልጸዋል። ባሕር ዳር የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኝዎችን ቀልብ የምትስብ፣ ጣና ፎረምን የመሳሰሉ ታላላቅ ሁነቶችንም የምታስተናግድ ውብ ከተማ ስለመኾኗም ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን