
አዲስ አበባ: መጋቢት 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ2017 የምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ሥትራቴጅክ፣ የሰቆጣ ቃልኪዳን የማሥፋፋት ምዕራፍ ትግበራ የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የጤና ሚኒስትር እና የምግብ ሥርዓት እና ኑትሬሽን የሚኒስትሮች ስትሪንግ ኮሚቴ የጋራ ሠብሣቢ ዶክተር መቅደስ ዳባ ባለፉት አራት ዓመታት በተሠሩ የትግበራ ሥራዎች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ 334 ወረዳዎች በሥርዓተ ምግብ ትግበራው ተካተዋል ብለዋል፡፡ ሚኒሰትሯ በ2018 ዓ.ም 186 ወረዳዎችን የትግበራው አካል ለማድረግ እየተሠራ መኾኑንም አንስተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ የሕጻናት ዕድገት ክትትል 80 በመቶ አፈጻጸም እንዳለው የገለጹት ዶክተር መቅደስ ዳባ ለ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እናቶች እና ሕጻናት የዕድገት ክትትል ተደርጓል ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በሁሉም ክልሎች ማኅበረሰቡን ያሳተፉ ሥራዎች በቅንጅት መሠራታቸውም ተነስቷል፡፡
በመድርኩ የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ እና ሥርዓተ ምግብ፣ የሰቆጣ ቃልኪዳን የስድስት ወራት አፈጻጻም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ስትሪንግ ኮሚቴው 15 ሚኒስትሮች የተካተቱበት ሲኾን በ2022 በኢትዮጵያ ከ2 ዓመት በታች ባሉ ሕጻናት የሚከሠትን መቀንጨር ለማስቀረት በሚሠሩ ተግባራት ላይ ይሳተፋሉ፡፡
ዘጋቢ፡- ቴዎድሮስ ኃይለኢየሱስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!