“ሰዎች ያለምንም ማመንታት ለሀገራቸው የሚበጀውን ሀሳብ ማዋጣት አለባቸው” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

17

ባሕር ዳር: መጋቢት 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ለሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ የቅድመ አጀንዳ ማሰባሰብ የግንዛቤ መፍጠሪያ የፓናል ውይይት በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በፓናል ውይይቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ጨምሮ ኮሚሽነሮች የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሚዲያ አካላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በፓናል ውይይቱ መልዕክት ያስተላለፉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ከመጭው ቅዳሜ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ ይከናወናል ብለዋል።

ለመጭው የኢትዮጵያ መልካም እጣ ፈንታ እየመከርን እንገኛለን ያሉት ፕሮፌሰሩ ሀገሪዊ ምክክሩ ሦስት ስትራቴጂካዊ የትኩረት ነጥቦች እንዳሉት አንስተዋል።

አካታች እና አሳታፊ ሀገራዊ ምክክር ማድረግ፤ የላቀ የማኅበረሰብ ተሳትፎ እና ንቅናቄ እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት እና ትስስር መሠረታዊ ነጥቦች ናቸው ነው ያሉት።

አብዛኞቹ ክልሎች አጀንዳቸውን መሰብሰባቸውን ተናግረዋል። በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል የጀንዳ ማሰባሰብ ሥራውን ለማከናወንም ጥረት እየተደረገ መኾኑንም ገልጸዋል።

“ሰዎች ያለምንም ስጋት እና ያለምንም ማመንታት ለሀገራቸው የሚበጀውን ሃሳብ ማዋጣት ያለባቸው ጊዜ አሁን ነው” ብለዋል። በግልጽ እና ፊት ለፊት ለመጻኢ ዕድል መመካከር ያስፈልጋል ነው ያሉት።

በአማራ ክልል በቀጣይ ቀናት የሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ውጤታማ እንዲኾን ሁሉም ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የኮሚሽኑን የሦስት ዓመት የሥራ ሥራው አልጋ በአልጋ እንዳልነበር አንስተዋል። ባለፉት ዓመታት ሰፋፊ ተግባራት መከናዎናቸውንም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየአማራ ክልል አስተዋጽኦ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ፦
Next articleዳሽን ቢራ ፋብሪካ ከንጋት ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር 25 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብ ዱቄት ድጋፍ አደረገ።