
ባሕር ዳር: መጋቢት 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ የመጣበትን እና የሕዳሴ ግድብ የተጀመረበትን ቀን መጋቢት 24 አስመልክቶ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው።
መጋቢት 24 በኢትዮጵያውያን ዘንድ በሁለት ዐበይት ጉዳዮች ትታወሳለች። በሕዝባዊ ፍላጎት የሥርዓት ለውጥ የመጣባት እና የአፍሪካውያን ኩራት የኾነው የሕዳሴ ግድብ የተጀመረባት ቀን ስለኾነች።
ይህችን ቀን የሚያስቡ ዜጎች በኢትዮጵያ በበርካታ ከተሞች ላይ ሰልፍ ወጥተው የለውጡ ሂደቶችን እንደሚደግፉ እየገለጹ ነው። በሰልፉ የተጀመሩ ሀገራዊ ለውጦች እና ኢትዮጵያን የማሳደግ ራዕዮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠይቀዋል።
እንደ ሀገር የተጀመሩ ታላላቅ የልማት ሥራዎች፣ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያንን አንድ የሚያደርጉ፣ የሚያሰባስቡ፣ በጋራ ዓላማ የሚያሰልፉ እሳቤዎችም የበለጠ ፍሬ እንዲያፈሩ በጋራ እንደሚቆሙ ሰልፈኞቹ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ለውጡ እውን ከኾነ ወዲህ የተመዘገቡ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ድሎችን ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በጋራ ለመቆም ዝግጁ መኾናቸውን አስታውቀዋል።
“የጋራ ማንነት ግንባታ ለብሩህ ኢትዮጵያችን፣ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን ለአዎንታዊ ሰላማችን፣ መጋቢት የቀጣዩ አርበኝነት ጅማሮ ማብሰሪያ፣ አብረን ጀምረናል አብረን እንደርሳለን” የሚሉ መልዕክቶችንም ሰልፈኞቹ አሰምተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!