የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) የልማት ሥራዎችን ለመመልከት ባሕር ዳር ከተማ ገቡ።

39

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) እና ሌሎች የፌዴራል መንግሥት መሪዎች ባሕር ዳር ገብተዋል።

መሪዎች ባሕር ዳር ከተማ ሲደርሱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

መሪዎች በቆይታቸው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ይመለከታሉ። እንደ ክልል በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ዙሪያም ከክልሉ መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ ውስጥ ትናንት እየራቀ፣ ነገ እየቀረበ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleሀገራዊ ለውጡ የመጣበትን እና የሕዳሴ ግድብ የተጀመረበትን ቀን አስመልክቶ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ነው።