በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች አቀባበል ተደረገላቸው።

60

ባሕር ዳር: መጋቢት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር በደዋ ጨፋ ወረዳ ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለዋል።

በትግል ስሙ ሌንጨ ቦሰና (አህሙዬ) የሚባለው የቡድኑ መሪ በተለምዶ ኦዳ ገራዶ በሚባለው ቦታ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ምክትል አሥተዳዳሪና የሰላምና ደኅንነት መምሪያ ኀላፊ አብዱ ጀማል መድሳኒ፣ የብልጽግና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ጀማል አሊ፣ እንዲኹም የዞኑ የሰላም ካውንስል አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት እጅ ሰጥተዋል።

አህሙዬ ያሳለፈው የትጥቅ ትግል ስህተት እንደነበር እና የገዛ ማኅበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ እንደነበር በመግለጽ ወደ ፊትም ሕዝቡን ለመካስ ዝግጁ መኾኑን በቁጭት ተናግሯል።

እስከ አኹን በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከ350 በላይ ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መግባታቸውን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሰላምና ደኅንነት መምሪያ መረጃ ያመላክታል።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ምክትል አሥተዳዳሪና የሰላምና ደኅንነት መምሪያ ኀላፊ አብዱ ጀማል መድሳኒ እንዳሉት ዘላቂነት ያለው ሰላም ለማረጋገጥ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ እንዳለ ገልጸዋል።

ዋናው ሥራ ታጥቀው በጫካ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የጥፋት ኀይሎችን በሰላማዊ መንገድ እጅ እዲሰጡ ማድረግ ሲኾን በዚህ ተግባርም ከፍተኛ ውጤት እየመጣ ነው፤ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleወጣቶች የሀገራቸውን ብዝኃ ማንነት፣ ታሪክ እና ባሕል በማወቅ የሕዝቦችን አብሮነት እንዲያጠናክሩ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) አሳሰቡ።
Next articleኩራታችን የኾነው የሕዳሴ ግድብ የመጨረሻችን መኾን የለበትም።