
ባሕር ዳር: መጋቢት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በተወሰኑ ውሳኔዎች እና በተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ የወጣቶች ክንፍ አባላት ሚና ላይ የሚመክር መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ሕዝቦች የቆዩ ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችሉ እና የዴሞክራሲ ልምምድን የሚያሰፉ በርካታ ሥራዎችን አከናውኗል ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ሀገራዊ ለውጡን በአግባቡ በመምራት በየጊዜው እየታረመ የሚልቅ የፖለቲካ ምህዳርን በመፍጠር ለሁሉም በሁሉም የኾነ ሥርዓት ለመገንባት እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል። ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል። ወጣቶች የአብሮነትን፣ የወንድማማችነትን እና የእህትማማችነትን ጉልበት በሕዝብ ውስጥ እንዲገለጽ መሥራት እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።
ወጣቶች የሀገራቸውን ብዝኃ ማንነት፣ ታሪክ እና ባሕል በማወቅ የሕዝቦችን አብሮነት እንዲያጠናክሩም አሳስበዋል። በሀገርም ኾነ በክልሉ ዘላቂ ሰላምን፣ ደኅንነትን እና ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ትግል ወጣቶች አይተኬ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ነው የተናገሩት። የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉጌታ አቤ ወጣቶች የከተማውን ሰላም እና ልማት በማረጋገጥ በኩል አይተኬ ሚናን እንየተወጡ ነው ብለዋል።
በከተማዋ ከጽንፈኝነት ነጻ የኾነ እና ጽንፈኝነትን የሚታገል ወጣት እንደተፈጠረም አብራርተዋል። ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሐፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከመሪዎች ጋር የአመለካከት እና የተግባር አንድነት ያላቸው፣ ውይይት እና ምክክርን የሚያስቀድሙ፣ ለሰላማዊ የፖለቲካ ባሕል የሚተጉ እና ለለውጥ የሚታትሩ ወጣቶች መፈጠራቸውን ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
