ወጣቶች በሁሉም ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ በማጎልበት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።

30

ደብረ ብርሃን: መጋቢት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ” ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የውሳኔ አቅጣጫዎች እና የወጣቶች ክንፍ ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት፣ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ምክር ቤት አባል እና በፓርቲው የአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት የወጣት ክንፍ ኀላፊ ሄለን ለገሰ፣ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ምክር ቤት አባል እና በፓርቲው የአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት የወጣት ክንፍ ኀላፊ ማቲያስ ጌታቸው እና ከደብረ ብርሃን ከተማ የተውጣጡ ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ፓርቲው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡ በሂደቱ ወጣቶች በሁሉም ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎ በማጎልበት ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ላይ የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ለከተማዋ የሰላም መስፈን እና የልማት ዕድገት ወጣቶች የሚያደርጉት አበርክቶ ጉልህ መሆኑንም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፉዎች ሰላምን በማረጋገጥ ሂደት ወጣቶች ለሚያደርጉት ጥረት የቅርብ እገዛ መደረግ እንዳለበት አንስተዋል፡፡ በልማት ዘርፎች ወጣቶችን በማሳተፍ ዘለቄታዊና አካታች ዕድገት በማምጣት በኩል የበለጠ ሥራዎች እንዲከናወኑም ጠይቀዋል፡፡

ለልዩነትና አለመግባባት መነሻ የሚሆኑ የሀሰተኛ መረጃ ሥርጭቶችን በመካከል በኩል ከወጣቶች ብዙ እንደሚጠበቅም በውይይቱ ተነስቷል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል አሲዳማ የእርሻ መሬትን በኖራ ለማከም የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ተዘጋጀ።
Next articleወጣቶች የሀገራቸውን ብዝኃ ማንነት፣ ታሪክ እና ባሕል በማወቅ የሕዝቦችን አብሮነት እንዲያጠናክሩ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) አሳሰቡ።