ምክር ቤቱ የፌደራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣውን የማሻሻያ አዋጅ አጸደቀ።

38

አዲስ አበባ: መጋቢት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚደነግገውን የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 22ተኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሂዷል። በጉባኤው የፌደራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበት ሥርዓት ለመደንገግ የወጣውን የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ መርምሯል አጽድቋል።

ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የፌደራል መንግሥት ክልሎች ከአቅም በላይ የሆነ የጸጥታ ችግር ሲያጋጥማቸው ጣልቃ የሚገባበትን፣ ጊዜያዊ አሥተዳደር ማቋቋም በሚያስችለው አንቀጽ ውስጥ የቆይታ ጊዜውን እና በምን ሁኔታ ይወሰናል የሚለዉን የሚያካትት ነው ተብሏል።

የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ 1373/2017 ኾኖ በሁለት ድምጽ ተዓቅቦ በአብለጫ ድምፅ ጸድቋል።

ዘጋቢ:- ኤልሳ ጉዕሽ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን ሥራ አስጀመረ።
Next articleበአማራ ክልል የአጀንዳ ማሠባሠብ ሥራዎች ላይ ሁሉም በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበ።