የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን ሥራ አስጀመረ።

45

አዲስ አበባ: መጋቢት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ በትራንስፖርት እጥረት ረጃጅም ሰልፎችን መመልከት የተለመደ ነው። ከተማ አሥተዳደሩ ችግሩን ለመቅረፍ ያስችላል ያለውን 100 በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ሥራ አስጀምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማ አሥተዳደሩ 100 ተሽከረካሪዎችን ገዝቶ ያቀረበ ሲኾን በሚገባ ለማሥተዳደር ለግል ባለሃብት መሰጠቱን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባን የትራንስፖርት ፍሰት ለማቀላጠፍ ተሽከርካሪ ገዝቶ ማቅረብ ብቻ በቂ ባለመኾኑ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የባለሃብቱ ተሳትፎ የላቀ መኾን አለበት ነው ያሉት።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኀላፊ ያብባል አዲስ በከተማ አሥተዳደሩ የትራንስፖርት ፍሰቱን ለማቀላጠፍ ከተሽከርካሪ አቅርቦት ባለፈ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት የማስፋፋት ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ.ር) የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በትራንስፖርት እጥረት ጊዜያቸውን ሊያጠፉ አይገባም ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ የጀመሩ ተሽከርካሪዎችም የተቀላጠፈ ትራንስፖርት እንዲኖር አጋዥ ይኾናሉ ነው ያሉት።

በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችም ከብዝሃ ሕይዎት ጋር የተስማሙ መኾናቸው የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ያላቸው ሚና የላቀ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ: ተመስገን ዳረጎት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአድማ መከላከል አባላት በደብረብርሃን ከተማ አቀባበል ተደረገላቸው።
Next articleምክር ቤቱ የፌደራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣውን የማሻሻያ አዋጅ አጸደቀ።