
አዲስ አበባ: መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 446ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ የማዕድ ማጋራት ተካሄዷል።
የማዕድ ማጋራቱ በከተማው ሁሉም ክፍለ ከተሞች ባሉ የምገባ ማዕከላት ተካሂዷል።
በቦሌ ክፍለ ከተማ በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በመገኘት የማዕድ ማጋራት ያካሄዱት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ለ1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሥተላልፈዋል።
በረመዳን ወርም ገቢያቸው ዝቅተኛ ለኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ምገባ መካሄዱን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ ተመስገን ዳረጎት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!