የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

26

ባሕር ዳር: መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 446ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከተቱ ሁሉ ምስጋና አቅርቧል።

ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው

ለመላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎች፣ ለወጣቶች እና ከበዓሉ ዋዜማ ጀምረው የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡ የጸጥታ ኃይሎችም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል ብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር የመረዳዳት እሴቶችን በማጎልበት ሊኾን እንደሚገባ የከሚሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አሳሰበ።
Next articleየአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት ሥነ ሥርዓት አካሄደ።