ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር የመረዳዳት እሴቶችን በማጎልበት ሊኾን እንደሚገባ የከሚሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አሳሰበ።

25

ከሚሴ: መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በከሚሴ ከተማ ተከብሯል።

ሕዝበ ሙስሊሙ የመረዳዳት እሴቶችን በማጎልበት የዒድ አልፈጥር በዓልን ሊያከብር እንደሚገባ የከሚሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ ሁሴን አሊ አሳስበዋል።

አቅመ ደካሞችና የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት ዘካተል ፊጥር በወቅቱ በመስጠት በዓሉን ተደስተው እንዲውሉ የሚያዝ በዓል መኾኑንም ተናግረዋል።

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከር ሰላሙን በመጠበቅና አብሮነቱን በማጠናከር ሊያከብር ይገባልም ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወቅት ያሳየውን የአብሮነት እሴት በማጠናከር በበዓሉም መተጋገዙን አስጠብቆ እንዲያከብር አሳስበዋል።

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሰላምን ለማፅናት የተሠሩ ሥራዎች ውጤት ማምጣታቸውን የገለጹት አሥተዳደሪው ዘላቂ ሰላም እንዲጸና ሕዝበ ሙስሊሙ የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

የበዓሉ ተሳታፊዎች በዓሉን በመረዳዳትና በመደጋገፍ እያሳለፉ መኾኑን ገልጸዋል።

ዘጋቢ :- ይማም ኢብራሂም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሃይማኖት ተቋማትን ማጠናከር በሥነ ምግባር የተገራ ትውልድ ማፍራት የሚያስችል መኾኑ ተመላከተ።
Next articleየዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።