
ደብረ ብርሃን፡ መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ ተከብሯል። የዒድ ሶላቱ ከተማ አስተዳደሩ በሰጠው ቦታ ተከብሯል።
በዓሉ ከማለዳ ጀምሮ ዘካትል ፊጥር በማውጣት ከዚያም በመስገጃ ቦታ ተክቢራ፣ ሶላት እና ሂትባ በመከወን የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል።
የረመዷን ወር ሃይማኖታዊ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት በዱዓ እና መልካም ተግባራትን በማከናወን ማሳለፋቸውን በበዓሉ አከባበር ላይ የተገኙት የሃይማኖቱ ተከታዮች ተናግረዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ለሃይማኖቱ ተከታዮች በሰጠው 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የዒድ ሶላቱ ተከናውኗል።
የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ለበዓሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የከተማ አሥተዳደሩ ለሃይማኖቱ ተከታዮች ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
የሃይማኖት ተቋማትን ማጠናከር በሥነ ምግባር የተገራ ትውልድ ማፍራት የሚያስችል በመኾኑ ከተማ አሥተዳደሩ ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ለዓለም ለይኩን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!