አብሮነት እና መተሳሰብን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር አሳሰበ።

14

ደብረ ታቦር: መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በደብረ ታቦር ከተማ ተከብሯል።

በዓሉ ፍቅር፣ አብሮነት እና መተሳሰብ ይበልጥ ጎልተው የሚታዩበት እና የታዩበት እንደኾነ የደብረ ታቦር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ አሕመድ ካሳ ተናግረዋል። ረመዳን የእዝነት ወር በመኾኑ በኢባዳ ያሳለፍነውን ጊዜ ማስቀጠል ይገባልም ብለዋል።

ሃሳባቸውን የሰጡን የሃይማኖቱ ተከታዮች በዓሉ ፍቅር፣ አብሮነት እና መተሳሰብ ይበልጥ ጎልተው የሚታዩበት መኾኑን በማንሳት የዘንድሮው በዓልም በእነዚህ መልካም ዕሴቶች መከበሩን ተናግረዋል።

የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን በበዓሉ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሳተላልፈዋል። በመልዕክታቸው “አብሮነት እና መተሳሰብን አጠንክረን እና የቀደመ እሴቶቻችንን አጉልተን ማስቀጠል አለብን” ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሕዝብ ጥያቄ በመመለሱ የጎንደር ከተማ እስልምና ምክር ቤት ምሥጋና አቀረበ።
Next articleአቅም ያጡትን በማሰብ መርዳት እና መደገፍ የሃይማኖቱ ግዴታ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሸሪዓ ፍርድ ቤት ሠብሣቢ ሼህ ወለላው ሰይድ ገለጹ።