
ጎንደር፡ መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዒድ አልፈጥር በዓል በጎንደር ከተማ ተከብሯል።
የጎንደር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሠብሣቢ ሐጂ አንዋር ቃሲም ረመዳን ሰብዓዊነትን አጉልተን የምናሳይበት ቀን ነው ብለዋል።
ከተማ አሥተዳደሩ የሙስሊሙ ኀብረተሰብ ላቀረበው ጥያቄ ለሰጠው ምላሽ ምሥጋና አቅርበዋል።
በከተማዋ የሽንታ ዳብርቃ የሕጻናት ትምህርት ቤት አካባቢ በሕገወጥ መንገድ ኮንቲነሮች ተቀምጠውበት ለ17 ዓመት ምላሽ አጥቶ የቆየ ቦታን የከተማ አሥተዳደሩ በወሰደው ሕግ የማስከበር ሥራ ቦታው ምላሽ ማግኘቱን ተናግረዋል። ለዚህም ምሥጋና አቅርበዋል።
በከተማዋ የተጀመሩ መሠረተ ልማቶች እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሰላምን ለማጽናት ትልቅ ድርሻ አላቸው ነው ያሉት።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው የከተማ አሥተዳደሩ አብሮነት እና አንድነትን በማጽናት በሕዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንደሚሠራ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!