“በረመዳን ጾም ወቅት የነበረዉ መረዳዳት እና መተሳሰብ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል” የመንግሥት ኮሙዩኬሽን አገልግሎት

21

ባሕር ዳር: መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሥተላልፏል።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባስተላለፈው መልዕክት ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 446ኛዉ የኢድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ ብሏል።

በረመዳን ጾም ወቅት የነበረዉ መረዳዳት እና መተሳሰብ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያለው በመልዕክቱ።

በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በልዩ ትኩረት እና ጉጉት የሚጠበቀው የረመዳን ወር ዘንድሮም በአማረና በደመቀ መልኩ ወንድማማችነትን እና እኅትማማችነትን አጠናክሮ ተጠናቅቋል ብሏል።

በዚህ መሠረት ዛሬ የኢድ አል ፈጥር በዓል በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል ነው ያለው።

በጾሙ ወቅት የነበረዉ እዝነት፣ መተሳስብና መዓድ ማጋራት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ባሕል ኾኖ መቀጠል የሚገባው ድንቅ ተግባር መኾኑንም አመላክቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዒድ አል ፈጥር በዓል በኮምቦልቻ ከተማ እየተከበረ ነው።
Next article“የጎንደርን ከፍታ ለማስቀጠል አብሮነትን ማጠናከር ያስፈልጋል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው