የዒድ አል ፈጥር በዓል በኮምቦልቻ ከተማ እየተከበረ ነው።

21

ደሴ፡ መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በኮምቦልቻ ከተማ የሃይማኖቱ አባቶች እና ተከታዮች በተገኙበት በሃይማኖታዊ ሥርዓት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ሙሃመድአሚን የሱፍ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ እና በመጠየቅ አብሮነታችንን በማሳየት ሊኾን ይገባል ብለዋል።

በመልዕክታቸውም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለከተማዋ ሰላም መኾን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።

በቀጣይም ሰላሙን በማስቀጠል አብሮነትን እና ወንድማማችነትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አመላክተዋል።

ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article” ቃል በገባነው መሠረት ቃላችን ጠብቀን አስረክበናል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው
Next article“በረመዳን ጾም ወቅት የነበረዉ መረዳዳት እና መተሳሰብ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል” የመንግሥት ኮሙዩኬሽን አገልግሎት