የባሕር ዳር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምስጋና አቀረበ።

31

ባሕር ዳር: መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከተማ አሥተዳደሩ ለሠጠው መስገጃ ቦታ ምስጋና አቅርቧል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሙሐመድ ዑስማን ላለፉት 20 ዓመታት በሕዝበ ሙስሊሙ ሲጠየቅ የቆየው የመስገጃ ቦታ ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ ካርታ መረከባቸውን ገልጸዋል። ቦታው በአጭር ጊዜ ለዒድ ሶላት እንዲውል ዝግጁ መደረጉንም ገልጸዋል።

ከተማ አሥተዳደሩ ሕዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸውን ጥያቄዎች እንደፈታው ሁሉ በቀጣይም አሁን ያለውን የሃይማኖቱ ተከታዮችን የሚመጥን የመስገጃ፣ የመቃብር እና የመስጅድ ቦታዎችን የካርታ እና ፕላን ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ሕዝበ ሙስሊሙ በሰላም፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎች የራሱን አሻራ እንዲያሳርፍ፣ በዓሉንም ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ለተቸገሩ ሁሉ በማካፈል እንዲያከብር አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለሀገራችን ሰላም ዱዓችንን መቀጠል አለብን” ሼህ ጀውሃር ሙሐመድ
Next article” ቃል በገባነው መሠረት ቃላችን ጠብቀን አስረክበናል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው