“ለሀገራችን ሰላም ዱዓችንን መቀጠል አለብን” ሼህ ጀውሃር ሙሐመድ

33

ባሕር ዳር: መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በባሕር ዳር ከተማ እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ጀውሃር ሙሐመድ እንኳን ለ1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የመስገጃ ቦታ በመስጠቱ ምስጋና ይገባዋል ነው ያሉት። ለከተማዋ መሪዎችም ምስጋና አቅርበዋል።

ለሙስሊሞች የተሰጠው ቦታ ደስታን የሚሰጥ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ይህም አንድነትን፣ አብሮ መኾንን፣ መተጋገዝን፣ ለሚመጣው ነገር ሁሉ አንድ ኾኖ መሰለፍን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

“ለሀገራችን ሰላም ዱዓችንን መቀጠል አለብን” ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው። የዒድ በዓልን ስናከብር በችግር ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችን በደመገፍ መኾን አለበት ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ሼህ ጀውሃር ሙሐመድ በበዓሉ ቀን ደካሞች በደስታ እንዲውሉ ማድረግ የሁሉም ድርሻ መኾኑንም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዒድ ሲከበር የኢትዮጵያዊያንን የአብሮነት እና የመረዳዳት መልካም እሴቶች በማንፀባረቅ ሊኾን እንደሚገባ የእስልምና ሃይማኖት አባቶች ተናገሩ።
Next articleየባሕር ዳር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምስጋና አቀረበ።