
አዲስ አበባ፡ መጋቢት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 446ኛ የዒድ አል ፈጥር በዓል በአዳማ ከተማ ዑመር መስጊድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክንውኖች እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ አሚኮ ያነጋገራቸው የአዳማ ከተማ የእስልምና ሃይማኖት አባቶች ዒድ ሲከበር የኢትዮጵያዊያንን የአብሮነት እና የመረዳዳት መልካም እሴቶች በማንፀባረቅ ሊኾን እንደሚገባ ተናግረዋል።
የሃይማኖት አባቶች እና የበዓሉ ታዳሚዎች ረመዳንን በፆም፣ በፀሎት፣ በስግደት እና ይቅር በመባባል አሳልፈናል ነው ያሉት።
ዒድ ደግሞ ደስታችን በመኾኑ ዘካ እና ዘካትልፍጥር በማውጣት በአብሮነት ብሎም በአንድነት የምናከብረው በዓል ነው ብለዋል።
ሀዘንም ኾነ ደስታ የሚያምረው ሀገር ሰላም ሲኾን ነው የሚሉት የሃይማኖቱ አባቶች ይህ ይሆን ዘንድ ከሌሎች የሃይማኖት ተከታዮች ጋር በጋራ ለሰላም እንሠራለን ብለዋል።
ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!