
በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በዝቋላ፣ ደሃና እና ሌሎች ወረዳዎች ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ተግባር ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ይገኛል፡፡
አካባቢው ዝናብ አጠር በመኾኑ የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ተግባርን ይሻል፡፡ በተጨማሪም የተከዜን ተፋሰስ በመስኖ የማልማት ሥራም በየደረጃው የሚገኝ አመራር እና የአካባቢው ማኅበረሰብ ርብርብን የሚጠይቅ ነው።
እነዚህን ተስፋ ሰጭ ጅምር ሥራዎች ማጠናከር፣ ማስፋት እና በቀጣይነት መፈፀም ይገባናል። የብሔረሰብ አስተዳደሩ ጅምር ተግባራት ለሌሎች ዝናብ አጠር የሀገራችን አካባቢዎችም ትምህርት ሰጭ ናቸው።