1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የደሴ ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።

74

ደሴ: መጋቢት 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አሥተዳደር ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሰይድ አሊ በዓሉ በሰላም እንዲከበር የከተማው የጸጥታ መዋቅር ግብረ ኀይል አቋቁሞ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ተናግረዋል።

ከበዓሉ ዕለት አስቀድሞ የበዓል ግብይት ስለሚከናወን ማኅበረሰቡ ከሀሰተኛ የገንዘብ ዝውውር እና ከሌሎች የማጭበርበር ተግባራት ራሱን እንዲጠብቅም አሳስበዋል።

በዓሉን ተገን በማድረግ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠርም ከደሴ ከተማ አሥተዳደር ንግድ መምሪያ ጋር ግብረ ኀይል ተቋቁሞ እየተሠራ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።

በበዓላት ወቅት ከፍተኛ የኀይል ተጠቃሚነት ፍላጎት ስላለ የእሳት አደጋ እንዳይከሰትም መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ማኅበረሰቡም በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለመደውን ትብብር እንደሚያደርግ አምናለሁ ያሉት ኀላፊው ችግሮች ካጋጠሙትም ለጸጥታ መዋቅሩ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ:- ከድር አሊ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጡት ካንሰር መንስኤ እና መፍትሔዎቹ
Next articleየሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት የጤናማ ቤተሰብ መሠረታዊ ጉዳይ መኾኑን የጤና ባለሙያዎች ተናገሩ።