ክሎኒንግ አለያም ስዋፒንግ ምንድን ነው?

23

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በርካታ አዳዲስ ነገሮችን አስተዋውቆናል። ከእነዚህ መካከል አንዱ ክሎኒንግ ነው። ክሎኒንግ የሚለው ቃልም የተለመደ እየኾነ መጥቷል። የቃሉ ጥሬ ትርጓሜ ለአንድ ነገር ተመሳሳይ ቅጂ የመፍጠር ሂደት ነው፡ ፡

ቃሉ ከቴክኖሎጂ ባሻገር በሥነ ሕይወትም የህዋስን ጄኔቲካዊ ቅጂ ከመፍጠር ጋር ተያይዞ ሲገለጽ እንሰማለን። ዲጂታል ክሎኒንግ ደግሞ ለምሥሎች፣ ድምጾች እና ቪዲዮዎች ተመሳሳይ ቅጃቸውን መፍጠር ነው።

ክሎኒንግ በዲጂታል ዓለም የሰዎችን ማንነት በአዲስ መልክ በመግለጽ፣ የመዝናኛውን ኢንዱስትሪ በማዘመን፣ በሥራ መሥክ ስጋቶችን እና በረከቶችን በመፍጠር፣ ባሕላዊ እና ማኅበራዊ ኹኔታዎችን በማቀራረብ እና ታሪክን በመሰነድ አገልግሎት ላይ ይውላል። ክሎኒንግ በዲፕፊክ ውስጥ ያለ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የፈጠረው የቴክኖሎጂ ውጤት ሲኾን የምስል ቅጂን የመፍጠር ሂደትን ስዋፒንግ እንለዋለን። ለድምጽ ከኾነ ደግሞ የድምጽ ክሎኒንግ ይባላል።

ብዙ ጊዜ የምስል ቅጂን ለመዝናኛ፣ የሰዎችን ምሥል ላልተፈላገ ዓላማ ለመጠቀም እና የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመልቀቅ ይጠቀሙበታል። የድምጽ ክሎኒንግ የአንድን ሰው ድምጽ አስመስሎ የእውነትም ይኹን የሐሰት መረጃዎችን ለማጋራት፣ ለመዝናኛ አገልግሎት እና ያለፈን ታሪክ በአዲስ ምናባዊ አቀራረብ ለማቅረብ ሲባል አገልግሎት ላይ ሊውል ይችላል።

ይህን ቴክኖሎጂ ወደ ተሻለ ደረጃ በማሳደግ ረገድ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የላቀ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ቴክኖሎጅው ከማደጉ ጋር ተያይዞ በክሎኒንግ የሚፈጠሩ የሐሰት መረጃዎች ሰዎች ለመለየት እስከሚያዳግታቸው ድረስ የሚፈትኑ ኾነዋል። በመኾኑም በዚህ መንገድ የተፈጠረ የሐሰት መረጃን መለየት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ያስፈልጋል።

ለልየታ ከሚያገለግሉ የቴክኖሎጂ አማራጮች ውስጥ ሪያሊቲ ዲፌንደር፣ ሴንቲኔል እና ኢቴስቲቪ የሚባሉ መለያ አማራጮችን ልንጠቀም እንችላለን።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article‎ሀዋሳ ከተማ የፊቼ ጫምባላላ በዓልን በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር ዝግጅቷን አጠናቅቃ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው።
Next article“ፖሊስ ለሕዝብ የገባውን ቃል ኪዳን ጠብቆ ሢሠራ ታማኝነትን ያገኛል” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ።