“ባላችሁ ዕውቀት እና ክህሎት ብቻ ሳይኾን በመሰዋእትነት ጭምር ሀገርን የሚያስከብር የሙያ ባለቤት ናችሁ” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

78

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለተከታታይ ወራት ያሠለጠናቸውን 33ኛ ዙር ምልምል የአድማ መከላከል ሠልጣኞችን በብር ሸለቆ መሠረታዊ የውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት አስመርቋል።

በምረቃ መርሐግብሩ ላይ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀንን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ወሳኝ ለኾነው ክልላዊ እና ሀገራዊ ተልዕኮ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። ” ባላችሁ ዕውቀት እና ክህሎት ብቻ ሳይኾን በመሰዋእትነት ጭምር ሀገርን የሚያስከብር የሙያ ባለቤት ናችሁ” ነው ያሉት። ሥልጠናውን በውጤታማነት ላስፈጸሙ አካላትም ምሥጋና አቅርበዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀን ተመራቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። ሰላም ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት እና ልማት ወሳኝ እና ቀዳሚ ጉዳይ መኾኑንም ተናግረዋል። በሥልጠና ያገኙትን ዕውቀት እና ሙያ ተጠቅመው የዜጎችን ደኅንነት በማስጠበቅ ፖሊሳዊ ግዴታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር አበበ ደለለ ለሠልጣኞች በሥልጠና ቆይታቸው በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የታገዘ ትምህርት መሰጠቱን ገልጸዋል። ሥልጠናው ሀገራዊ እና ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታውን በውል ተገንዝበው የሚሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ የሚያደርግ መኾኑንም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የአለ ፈለገ ሰላም የሥነ ጥበብ እና ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ።
Next article‎ሀዋሳ ከተማ የፊቼ ጫምባላላ በዓልን በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር ዝግጅቷን አጠናቅቃ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው።