
ባሕርዳር፡ መጋቢት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን 33ኛ ዙር የአድማ መከላከል ሠልጣኞችን በብርሸለቆ እያስመረቀ ነው።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ እና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን ጨምሮ የሀገር መከላከል ሠራዊት የጦር መኮንኖች እና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የተቋሙን ዕሴቶች ተገንዝቦ ለተግባራዊነቱ የሚተጋ እና ውጤት የሚያሳይ ኀይል ሆኖ እንዲገኝ ያስቻለ ሥልጠና መኾኑን በምርቃቱ ወቅት ተመላክቷል። በጠራ አመለካከት፣ ስነ ምግባር እና ሙያዊ ክህሎት ሕዝብን ማገልገል እንደሚገባም ተገልጿል።
ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሕዝባዊነታቸውን በተግባር በማረጋገጥ የክልሉን ሕዝብ ከወንጀል ስጋት ነፃ የማድረግ ትልቅ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!