ሀገር አቀፍ የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ ማስተዋወቂያ መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

19

ባሕር ዳር: መጋቢት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገር አቀፍ የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ ማስተዋወቂያ መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) እስካኹን የነበረው የግብርና እና የገጠር ልማት ፖሊሲ አኹን ካለው ፍላጎት ጋር ባለመጣጣሙ እና አዳዲስ ሀሳቦች በመምጣታቸው አዲስ የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ በአዲስ መልክ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

የሕዝብን ዕድገት እና ፍላጎት የሚመጥን፣ እንደ ሀገር የሚጠበቀውን እና የሚታለመውን ዕድገት ለማሳካት ዘመኑን የሚዋጅ ፖሊሲ አስፈላጊ ነው ብለዋል። መድረኩ በአዲሱ ፖሊሲ ላይ ግልጽ በመኾን ሥራን በአግባቡ ለመሥራት እና ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleከአላማጣ – ኮምቦልቻ በተዘረጋው መስመር ላይ ብልሽት በመከሰቱ በአካባቢው ኃይል ተቋርጧል።
Next articleደጀን ወረዳ ለመኸር ምርት ከ77 ሺህ በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለማሰራጨት እየሠራ ነው።