ከአላማጣ – ኮምቦልቻ በተዘረጋው መስመር ላይ ብልሽት በመከሰቱ በአካባቢው ኃይል ተቋርጧል።

18

ባሕር ዳር: መጋቢት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከአላማጣ – ኮምቦልቻ በተዘረጋው ባለ230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ኃይል አስተላለፊ መስመር ላይ ብልሽት በማጋጠሙ በአካባቢው ላይ አገልግሎቱ ተቋርጧል። ከዶሮ ግብር ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎት ያገኙ በነበሩ ከተሞች ናቸው ኃይል የተቋረጠባቸው።

በዚህም መሰረት ወልድያ ከተማ ሙሉ በሙሉ፣ ሲሪንቃ፣ መርሳ፣ ጊራና፣ ውርጌሳ፣ ወልዲያ መቻሬ ውኃ፣ አመያ መጫ፣ ሮቢት፣ ጎብየ፣ ሀራ እና ጭፋራ አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦትቱ የተቋረጠባቸ አካባቢዎች መኾናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች ችግሩ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል በፍጥነት ተፈትቶ አገልግሎት እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁም አገልግሎቱ ጠይቋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደርን በማሻሻል የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እየተደረገ ነው።
Next articleሀገር አቀፍ የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ ማስተዋወቂያ መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።