የመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደርን በማሻሻል የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እየተደረገ ነው።

32

ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን የመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደር ሪፎርምን ለመተግበር የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጌታቸው ጀንበር (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለሥልጣናት፣ የዞን እና የወረዳ መሪዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ በየደረጃው የሚገኝ የመንግሥት አገልግሎት አሥተዳደርን በማሻሻል እና በማሳለጥ የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ18 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩን የደሴ ከተማ አሥተዳደር ሥራ እና ሥልጠና መምሪያ ገለጸ።
Next articleከአላማጣ – ኮምቦልቻ በተዘረጋው መስመር ላይ ብልሽት በመከሰቱ በአካባቢው ኃይል ተቋርጧል።