ሴቶች በሀገር ልማት እና በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ ቁልፍ ድርሻ እንዲኖራቸው ማድረግ ይገባል።

34

ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበራት ፌዴሬሽን የሥራ ማስጀመሪያ ንቅናቄ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በአማራ ክልል መንግሥት የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ መስፍን አበጀ (ዶ.ር) የሴቶች ፌዴሬሽን ነጻ ሐሳብ የሚያንሸራሽር በመኾኑ ለዴሞክራሲ ግንባታ የበኩሉን አይነተኛ ሚና ይጫዎታል ነው ያሉት።

ፌዴሬሽኑ በውስጡ የያዛቸውን ማኀበራት ጠንካራ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ በማድረግም በክልሉ ለሚኖሩ ሴቶች ተጠቃሚነት የራሱን ድርሻ መወጣት ይችላል ብለዋል።

ፌዴሬሽኑ የዴሞክራሲን የባሕል ልምምድ በማጎልበት የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት አቅም ያጠናክራልም ነው ያሉት።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች በሀገር ልማት እና በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ ቁልፍ ድርሻ እንዳላቸውም አስገንዝበዋል።

በኢኮኖሚ፣ በማኀበራዊ እና በፖለቲካው ዘርፍ የሚገባቸውን ድርሻ በመስጠት የሀገርን ብልጽግና ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት።

ሴቶች በየዘርፉ በተገቢው ሁኔታ ተደራጅተው በንቃት ሲሳተፉ፣ ሀሳብ ሲያዋጡ እና የመሪነት ሚናቸውን ሲወጡ ተጠቃሚነታቸው እንደሚረጋገጥ ገልጸዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙ ሴቶች ተሳትፏቸው ላቅ ሲል በሀገር አቀፍ ደረጃም የሚኖራቸው የተደማጭነት እና የውሳኔ ሰጭነት ሚናቸው ከፍተኛ ይኾናል ብለዋል።

ዘጋቢ:- ሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሥራ ዕድሎች ክህሎት መር እንዲኾኑ ለማድረግ እየሠራ መኾኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።
Next articleግጭት የትምህርት ስብራትን አስከትሏል።