የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኀይሌ (ዶ.ር) በአማራ ክልል የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ኮሚሽን የንቅናቄ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ባሕርዳር ገቡ።

33

ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኀይሌ (ዶ.ር) በአማራ ክልል የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ኮሚሽን የንቅናቄ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ባሕርዳር ገብተዋል።

ከኮሚሽነሩ ጋር የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጌታቸው ጀንበር (ዶ.ር) እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የሥራ ኀላፊዎቹ ባሕርዳር ሲገቡ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባንቻምላክ ገብረማርያም እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ ይካሄዳል። በንቅናቄ መድረኩ የተሠሩ ሥራዎችን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመምህራን ሥራቸውን እንዳይሠሩ እንቅፋት የሚኾኑ አካላት መወገዝ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዝዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ.ር) ገለጹ።
Next articleየኀይል ስርቆት በሕዝብ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እና የሕግ ተጠያቂነቱ?