የአማራ ክልል የትምህርት ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።

41

ባሕር ዳር: መጋቢት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የትምህርት ንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። በንቅናቄ መድረኩ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይረጋ ሲሳይ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር የክልሉን የትምህርት ተሳትፎ፣ ጥራትን እና ተደራሽነትን ጎድቶታል። በዛሬው የንቅናቄ መድረክ በክልሉ የትምህርት ዘርፍ በደረሰው ጉዳት ላይ በመምከር የቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአማራ ክልል የትምህርት ንቅናቄ ላይ ለመሳተፍ ባሕር ዳር ከተማ ገቡ።
Next article“ትምህርት ቅንጦት ሳይኾን መሠረታዊ ሰብዓዊ መብት ነው” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ