በምዕራብ ጎጃም ዞን በ481 ተፋሰሶች የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ ተሠርቷል።

24

ፍኖተ ሰላም: መጋቢት 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ የተጎሳቆሉ ተፋሰሶችን መልሶ በማልማት እና የእርሻ መሬት በጎርፍ እንዳይጋለጥ በማድረግ ለምነቱ እንዲጨምር አይነተኛ ሚና አለው።

በተለይም የአካባቢን ሥነ ምህዳር ከመጠበቅ በተጨማሪ ለአርሶ አደሮች በእንስሳት እርባታ፣ በንብ ማነብ እና በተለያዩ ዘርፎች የሥራ ዕድልም እየፈጠረ ነው።

በምዕራብ ጎጃም ዞን 526 ተፋሰሶች ላይ የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ ለማከናወን ታቅዶ 222 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ 481 ተፋሰሶችን ማልማት መቻሉን የዞኑ ግብርና መምሪያ ኀላፊ ተስፋዬ አስማረ ገልጸዋል።

ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙላት አዲስ በ4ሺህ 416 ሄክታር መሬት ላይ 74 ተፋሰሶችን የማልማት ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።

በተለይም በየጊዜው አርሶ አደሮች ለተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ ያላቸው ግንዛቤ እና ፋይዳው እየተሻሻለ በመምጣቱ በትኩረት እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።

በዚህም በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ከዚህ በፊት በተከናወነ የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ በአምስት ቀበሌዎች እየለሙ ባሉ ተፋሰሶች ላይ 3ሺህ 655 የማኅበረሰብ ክፍሎች በንብ ማነብ፣ በእንስሳት ማድለብ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ተጠቃሚ መኾናቸውን ኀላፊው ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሙሉ ትኩረታችን በጸረ ድህነት ትግል ላይ መኾን አለበት” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)
Next articleሳምንቱ በታሪክ