በጃቢ ጠህናን ወረዳ ለአርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያ እየተሰራጨ ነው።

25

ፍኖተ ሰላም: መጋቢት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምእራብ ጎጃም ዞን በጃቢ ጠህናን ወረዳ ለ2017/18 ዓ.ም የመኸር ምርት ዘመን 50 ሺህ 836 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን 259 ሺህ 538 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት መታቀዱን የገለጹት የጃቢ ጠህናን ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አስቻለ ሞሴ እስካሁን 28 ሺህ 878 ኩንታል በማሰራጫ ማዕከላት ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል።

በተለይም አርሶ አደሮ የአቅርቦት ችግር እንዳያጋጥማቸው እና በወቅቱ እንዲደርሳቸው ለማድረግ በቅንጅት እየተሠራ መኾኑንም አቶ አስቻለ ገልጸዋል።

የጃቢ ጠህናን ወረዳ ምክትል አሥተዳዳሪ የቻለ ይርጋ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ይስተዋሉ የነበሩ የፍትሐዊነት እና መዘግየት ችግሮችን ለመፍታት ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

የግብዓት ስርጭቱን ውጤታማ ለማድረግ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመኾን ሕገ ወጥነትን ለመከላከል በቅንጅት እየተሠራ ነው ብለዋል።

ካለው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ለአርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያውን በየቀበሌው ለማድረስ ትራንስፖርት መመቻቸቱን ነው አቶ የቻለ የተናገሩት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የሠራዊቱን አቅም የማሳደግና ፕሮፌሽናል ሠራዊት የመገንባት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
Next article“መምህር መግደል እንደ ጀግንነት፣ ትምህርት ማቋረጥ እንደ አርበኝነት”