
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አፋር ክልል በመገኘት የክልሉን የግብርና እና የኢንዱስትሪ አቅሞች የሚያሳዩ ቁልፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ጉብኝታቸው ከስድስት ወራት በፊት ምርት የጀመረውንና 15 ቶን በሰዓት የሚያመርተውን የአዮዳይዝድ ጨው ማምረቻ ምልከታን ያካተተ ነበር። በተጨማሪም በአፋር ክልል የተሳካ የበጋ ስንዴ ምርት እየተካሄደበት ያለውን ልማት ሥራ እና የአይሮላፍ መኖ ባንክ ልማት ማዕከልንም ጎብኝተዋል። በክልሉ ስላለው የግብርና አቅም የነበረውን የተሳሳተ ምልከታ በማሸነፍ በመስኖ የለማ አስደናቂ የስንዴ ምርት መገኘት ችሏል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ እንደሚያመላክተው ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ቀዳማዊት እመቤቷ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባውን እና ከማሳ ወደ ገበታ ሙሉ የምግብ ምርት ሰንሰለት የሚያጎላውን ዘመናዊ የዳቦ ፋብሪካም መርቀዋል። ፋብሪካው በተገጠሙለት ዘመናዊ ማሽኖች በመጠቀም 420 ኩንታል ስንዴ በቀን መፍጨት የሚችል ሲሆን 300,000 ዳቦዎችንም በ24 ሰዓታት ማምረት ይችላል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!