
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በመከላከያ ትምህርት እና ስልጠና መምሪያ የአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን የሜካናይዝድ ሙያተኞች በማስመረቅ ላይ ነው።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የመከላከያ የመረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪ እና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጀነራል አለምሸት ደግፌ፣ የመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮንን፣ የሜካናይዝድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ከፍያለው አምዴ እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አመራሮች እና አባላት ተገኝተዋል።
ሠልጣኞች በቆይታቸው በተግባር እና ንደፈ ሀሳብ በቂ እውቀት መጨበጣቸው ተገልጿል።
ኢዜአ እንደዘገበው በዚህም መደበኛ ሥርዓተ ትምህርቱ የሚሸፍነውን ቆይታ አጠናቀው ለምረቃ መብቃታቸው ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!