የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ተደራሽ እንዲኾን በትኩረት እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ገለጸ።

32

ባሕር ዳር: መጋቢት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኀላፊ በሪሁን መንግሥቱ በደቡብ ጎንደር ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ላይ እየተካሄደ ያለውን የማዳበሪያ ስርጭት በመስክ ተገኝተው ተመልክተዋል።

አቶ በሪሁን እንዳሉት ለክልሉ የሰላም፣ የልማት፣ የዴሞክራሲ እና የመልካም አሥተዳደር ሳንካ የኾነውን ታጣቂ ቡድን አሽቀንጥሮ ለመጣል ሁሉን አቀፍ እልህ አስጨራሽ ትግል በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአንድ በኩል የሕግ ማስከበር ሥራ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የልማት ሥራዎችን አጠናክረን እየቀጠልን ያሉት አቶ በሪሁን ቡድኑ ሰርጎ ከመሸገባቸው ቦታዎች እየተገፋ ወደ በረሀ እንዲገባ ተገዷል ብለዋል።

ቡድኑ ስጋት ከማይኾንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ጥምር ጦሩ የኦፕሬሽን ሥራዎችን በተቀናጀ መልኩ እያከናወነ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር ጦሩ በክልሉ እየገባ ያለውን የአፈር ማዳበሪያ ከዘራፊ ቡድኑ ጠብቆ ለአርሶ አደሮች ተደራሽ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

“በቀጣይም የሕዝቡን አንገብጋቢ ጥያቄ የኾነውን ሰላም እና ልማት ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመመለስ የጸጥታ መዋቅራችን በተከታታይ የመገንባት እና የማዘጋጀት ሥራ እየሠራን ነው ብለዋል” አቶ በሪሁን ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም ለአንድ ዓላማ ያሰለፈ ሀገር የምትኮራበት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው” አረጋዊ በርሄ (ዶ.ር)
Next articleሕዝብን በቅንነት ለማገልገል እንደሚሠሩ የወልድያ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ።