“አሚኮ ስሁት ትርክቶችን ለማረም እና ኅብረብሔራዊት ኢትየጵያን ለመገንባት እየሠራ ነው” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ

30

አዲስ አበባ: መጋቢት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት አሚኮ በአዲስ አበባ ያስገነባውን ስቱዲዮ ጎብኝተዋል፡፡ አሚኮ ዘመናዊና ግዙፋ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ለማስገንባት በአዲስ አበባ የተረከበውን መሬትም ተመልክተዋል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ሕዝብ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ጋር የሚያኖረው እሴት ያለው ሕዝብ ነው፤ በመኾኑም ክልሉ የተለያዩ ብሔሮችን በውስጡ አቅፎ ይዟል ብለዋል፡፡ የዚህ ትልቁ ማሳያ ደግሞ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በብዝኀ ቋንቋ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ስሁት ትርክቶችን ለማረም እና ኅብረብሔራዊት ኢትየጲያን ለመገንባት እየሠራ መኾኑን ጠቁመዋል፡፡

የአሚኮ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ምክትል ሥራ አሥፈጻሚ ሰጠኝ አቡሃይ አሚኮ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ አብሮነትና ወንድማማችነትን ለማጠናከር እየሠራ ነው ብለዋል። በዚህም ሀገራዊ እና አሕጉራዊ መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ በማድረስ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ኾኖ እያገለገለ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት አሚኮ በአዲስ አበባ ስቱዲዮ ዘመናዊና ተወዳዳሪነቱን የሚያልቁ ቴክኖሎጂዎች ባለቤት መኾኑን ገልጸዋል። ተቋሙ በ30 ዓመት ጉዞው እራሱን እያሳደገ ተደራሽነቱንም እያሰፋ የመጣ የሚዲያ ተቋም መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት የሚዲያ ተቋሙን ለማጠናከር እና ለማደገፍ የበኩሉን እንደሚወጣም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለብሔራዊ ፈተና ተገቢውን ዝግጅት እያደረጉ መኾኑን ተፈታኝ ተማሪዎች ተናገሩ።
Next article“የሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም ለአንድ ዓላማ ያሰለፈ ሀገር የምትኮራበት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው” አረጋዊ በርሄ (ዶ.ር)