“ብዝኀነት ለአፍሪካ መልኳም ታሪኳም ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

15

ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ኢትዮጵያ “ጥበብ እና ባሕል ለቀጣናዊ ትብብር” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደውን ሁለተኛውን የምስራቅ አፍሪካ የጥበባት እና ባሕል ፌስቲቫል፣ በውቧ መዲናችን እና በግዙፉ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በማስተናገዷ ታላቅ ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

የተለያዩ ቋንቋዎችን መናገር፣ በልዩ ልዩ ባሕሎች ውስጥ ማደግ፣ ከተለያዩ እምነቶች ጋር መኖር ለእኛ ለአፍሪካውያን ጌጣችን ነው ብለዋል፡፡ ሥሪታችን ብዝኀነት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕዝቦቻችን፣ ባሕሎቻችን እና ቋንቋዎቻችን ሰው ሠራሹን ድንበር ይሻገራሉ ነው ያሉት፡፡
አፍሪካዊት ሀገር ኢትዮጵያም የሰው ዘር መገኛ እና የኅብረ ባሕል እና የኅብረ ብሔር ማዕከል ናት ብለዋል፡፡

ሀገራችን በዚህ ዘርፍ ለቀጣናው ሀገራት ትስስር መጠናከር ትልቅ አስተዋፅዖ አበርክታለች፡፡ ይህ ደግሞ የባሕል ዲፕሎማሲ እና ቀጣናዊ ትሥሥር እንዲጎለብት አስቻይ ሁኔታን ፈጥሯል ነው ያሉት፡፡

የብዝኀ ባሕል ሃብቶች እና የጋራ መገለጫ የኾኑ ዕሴቶችን ለሕዝቦች አንድነት እና መግባባት፣ ለልማት እና ለዘላቂ ሰላም እንዲሁም ማኅበራዊ ትሥሥርን ለማጎልበት መጠቀም ይኖርብናልም ነው ያሉት፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጀግኒት ከሌላት ላይ ሊቀሟት የመጡ ሕገ ወጦችን በሕግ እጅ ላይ ጣለቻቸው።
Next articleትኩረት ያጣው የዐዕምሮ ጤና!