በዞኑ ያለውን እምቅ አቅምና ጸጋ በመጠቀም ለወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር እየሠራ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሥራ እና ሥልጠና መምሪያ አስታወቀ።

6

ደብረ ማርቆሥ: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሥራ እና ሥልጠና መምሪያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ27 ሺህ በላይ ሥራ ፈላጊዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት አቅዶ እየሠራ ይገኛል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በእቅድ ከተያዘው ውስጥ 51 በመቶ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። ይህም በግጭት ውስጥ ኾኖ ለሥራ ፈላጊዎች የሥራ እድል ለመፍጠር የተሄደበት እርቀት አበረታች መኾኑን የመምሪያው ኅላፊ ፀሐይ ቦጋለ ተናግረዋል።

ወጣቶች በየአካባቢው በሚከናወኑ ማኅበራዊ እና ልማታዊ ተግባራት ላይ በንቃት በመሳተፍ ራሳቸውን ለማሳደግ እንዲጥሩ ተጠይቋል። የመስሪያ እና የመሸጫ ቦታዎች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ እና በውላቸው መሠረት እንዲተላለፉ የማስተካከያ እርምጃዎች እየተወሰዱ መኾኑንም መምሪያ ኀላፊው አስገንዝበዋል።

አቶ ፀሐይ ከ2 ሺህ 600 መቶ በላይ የሚኾኑ ኢንተርፕራይዞችን ደረጃ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ስለመኾኑም ተናግረዋል። የቆዩ ብድሮች እንዲመለሱ በማድረግ እና ለአዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ብድር በመስጠት እንዲጠናከሩ እየተሠራ ነውም ብለዋል። በዞኑ ያለውን እምቅ አቅምና ፀጋ በመጠቀም በቀሪ ወራት በርካታ ወጣቶችን ቅድሚያ ሰጥቶ የሥራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑንም መምሪያ ኀላፊው ጠቁመዋል።

ወጣቶች በየአካባቢው በሚከናወኑ የማኅበራዊ የልማት እና ዲጅታላይዜሽን ተግባራት በንቃት በመሳተፍ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እና በዕውቀት ለማሳደግ መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም ኀላፊው አሳስበዋል።

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በዚህ በጀት ዓመት 4 ሺህ 300 የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ ዘርፎች በሥራ ላይ እንደሚገኙ ከዞኑ ሥራ እና ሥልጠና መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል የትምህርት ሥራ ላይ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በትኩረት መመካከር እንዳለበት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አሳሰቡ።
Next articleየአትክልት እና ፍራፍሬ ችግኞችን ለማቅረብ እየሠራ መኾኑን የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ አስታወቀ።