
ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያሄደ ነው፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን እና አስተያየት አቅርበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ የሕዳሴ ግድብ ብዙ ፈተና የታየበት፣ አንድም ብር ከውጭ ብድር ያልተገኘበት፣ ከወደብ እስከ ሕዳሴ ግድብ ድረስ ግብዓት አጅበን እየወሰድን የሠራነው ነው ብለዋል፡፡
በሕዳሴ ግድብ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በጋራ ሪቫን እንቆርጣለን ነው ያሉት፡፡
ሕዳሴ የመላው የአፍሪካ ኩራት ነው፤ ለመላው አፍሪካ መቻልን ያሳየንበት ነው፣ ሕዳሴ ስህተትንና በውስጣችን ያለውን ውድቀት ያረምንበት ነው ብለዋል።
አፍሪካውያን የራሳቸውን ሀብት በራሳቸው ዜጎች ማልማት እና መቀየር እንደሚችሉ በተግባር የሚያስተምር ሥራ ነውም ብለዋል፡፡
በሕዳሴ ሥራ ኩራት እና ክብር እንደሚሰማቸውም ተናግረዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!