“በምርት ዘመኑ 187 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ ነው” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)

25

ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በ2017/18 ምርት ዘመን የመኸር ሰብል ፓኬጅ የአሠልጣኞች ሥልጠና እና የዕቅድ ትውውቅ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየሰጠ ነው።

በሥልጠናው ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) ምርት እና ምርታማነትን ከሚጨምሩ ግብዓቶች አንዱ ከኾነው የአፈር ማዳበሪያ አጠቃቀም አንጻር አዲስ ፓኬጅ ለማስተዋወቅ ሥልጠናው ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

በ2017/18 የምርት ዘመን የመኸር ምርት 187 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።

በተለይ የምግብ ፍላጎትን እና ፍጆታ ለማረጋገጥ፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓት አቅርቦትን ለማሟላት እና ወደ ውጭ ሀገር የሚላኩና ምንዛሬ ሊያስገኙ የሚችሉ የሰብል ዓይነቶችን በዕቅዱ ለማምረት የሚያስችል ሥልጠና ነውም ብለዋል

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“መንግሥት ለትምህርት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“ነጻ አውጭ ነን ባዮች መጀመሪያ ተጎጂ የሚያደርጉት የራሳቸውን ሕዝብ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)