
ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 21ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያሄደ ነው፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን እና አስተያየት አቅርበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም በየአካባቢው የምንጋዋቸው ሰዎች አትማሩ፣ አትታከሙ፣ አትረሱ ከሚሉ ጋር ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
የምንዋጋቸው መድኃኒት አውጥተው የሚደፉ፣ ማዳበሪያ እንዳይደርስ የሚያደርጉ ነገር ግን ለሕዝብ የሚታገሉ ናቸው ብለዋል፡፡ ትምህርት ምን ያደርግላቸዋል ብለው የሚያስቡ ናቸው ነው ያሉት፡፡
በጩኸት እና በግርግር እውነት ለመደበቅ የሚደረግ ሙከራ ስላለ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ መኾኑን ነው የተናገሩት፡፡ መንግሥት ለትምህርት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡
በጤናው ዘርፍም በትኩረት እየተሠራ መኾኑን አንስተዋል፡፡ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ እንደሚሠራም ተናግረዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን