“በቀን 150 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ከወደብ እናጓጉዛለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

18

ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ሥብሠባውን እያካሄደ ነው፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸው መንግሥት ለማደበሪያ ድጎማ እያደረገ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡ 84 ቢሊዮን ብር ለማደበሪያ መደጎማቸውንም ተናግረዋል፡፡

በአንድ ኩንታል 3 ሺህ 700 ብር እንደጉማለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኛ ማዳበሪያ ስለማናመርት የማዳበሪያ ዋጋ መወሰን አንችልም ነው ያሉት፡፡ እኛ የምንችለው መደጎም ነው ብለዋል፡፡

72 ቢሊዮን ብር ለነዳጅ ድጎማ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡ በነዳጅ ከፍተኛ ድጎማ እየተደረገ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

እንደ ማደበሪያ ሁሉ ኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋንም መወሰን እንደማትችል የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜጎቿ እንዳይጎዱ ግን ትደጉማለች ነው ያሉት፡፡

መድኃኒት፣ ዘይት እና ሌሎችንም እንደሚደጉሙ አንስተዋል፡፡ ሁሉንም ደጉሞ ስለማይቻል መሥራት እና ማምረት ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡

24 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡ በቀን 150 ሺህ ኩንታል ማደበሪያ ከወደብ እናጓጉዛለን ነው ያሉት፡፡ በእያንዳንዱ አካባቢ ደግሞ በወታደር አጅበን እናደርሳለን ብለዋል፡፡

የማዳበሪያ ፋብሪካን ማቋቋም ካልቻልን በዚህ መቀጠል አንችልም ነው ያሉት፡፡ ሁለተኛው ሕዳሴያችን የሚኾነው የማዳበሪያ ፋብሪካን መሥራት ነው ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባለፉት ስምንት ወራት ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚኾኑ ሥራ ፈላጊዎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ።
Next article“መንግሥት ለትምህርት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)