3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የዕዳዳ ሸግሽግ መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ።

37

ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ከየትኛውም የሙሉ ዓመት የወጪ ንግድ ገቢ ይበልጣል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የነበረባትን ዕዳ ለመቀነስ ስንሟገት የነበረው ጉዳይ ፍሬ አፍርቶ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የእዳ ሸግሽግ አግኝታለች ብለዋል።

ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ በነበረው ድርድር የእዳ ሽግሽግ ለማድረግ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡

ገቢን በሚመለከት ባለፉት ስምንት ወራት ከ580 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸው ከወጪ አንጻር ሰፋፊ ድጎማዎች ስለተደረጉ ወጪው ከገቢያችን ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡

ገቢው ሙሉ በሙሉ ጪውን መሸፈን ባይችልም መጠነኛ መሻሻሎች ይታዩበታል ነው ያሉት፡፡

አሁንም ኢትዮጵያ እየሞከረች ያለችው ከጥቅል ሀገራዊ ምርቷ ሰባት በመቶ ገደማ ገቢ ለማስገባት መኾኑን አስታውቀዋል፡፡

ኬኒያ ከ15 ነጥብ 5 በላይ እንደምታስገባ ገልጸው፤ ገቢ ካልተሰበሰበ መሠረተ ልማት ይስፋፋ ማለት እንደማያስኬድ ተናግረዋል፡፡

በስምንት ወራት የተሠራውን በአራት ወር ከደገምነው ከፍተኛ የወጪ ንግድ የሚመዘገብበት ዓመት እንደሚኾን ጠቁመዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
Next article‘’የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ እምርታዊ ለውጥ አስመዝግቧል’’ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)