
ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ፦
✍️ “በግብርና ምርት የአነስተኛ አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ደርሷል፤
✍️ በበጋ መስኖ ልማት 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ተሸፍኗል፣
✍️ በዚህም ከ300 ሚሊየን ኩንታል ያላነሰ ምርት ይስበሰባል ተብሎ ይጠበቃል፤
✍️ በቡና እና ሻይ ምርትም የተሻለ ስኬት ተመዝግቧል፤
✍️ ባለፉት ስምት ወራት ብቻ ከቡና ወጪ ንግድ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፤
✍️ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የሰብ ሰሃራ ዕድገት 4 ነጥብ 2 ይኾናል ብለው ገምተው ነበር፤
✍️ ኢትዮጵያ 8 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ችላለች፤
✍️ የአነስተኛ አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን ከ17 ነጥብ 5 ሚሊዮን ወደ 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ማደግ ተችሏል፤
✍️ ዛሬ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ ስንዴ አምራች ሀገር ነች፤
✍️ በስንዴ ብቻ ሳይኾን በሌሎችም ዘርፎች የመጣው እምርታ ይበል ይቀጥል የሚያስብል ነው፤
✍️ ለምሳሌ ቡና በለውጡ ማግስት 700 ሚሊዮን ገደማ በዓመት ኤክስፖርት እናደርግ ነበር፤ በቡና ኤክስፖርት ባለፉት ስምንት ወራት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል፤
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!